Amharic

እኛ ማን ነን?

እኛ የቶሮንቶና አካባቢዋ ወጣት የሆንን ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ቡድን ነን ፣ በዚህች ከተማ ለብዙ ዓመታት የኖርን፣ የተማርን እና በማህበረሰባችን የታገዝን ፣ ብዙዎቻችን በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ግንባታ ውስጥ የተሳተፍን ሲሆን ለድጋፍ ባሳየናቸው ፍላጎቶች በቀጥታም የሚመልከተን ነን ፡፡ የጋራ ህልውና ፍላጎታችንን በማሟላት ላይ የሚያተኩር የጋራ ዕርዳታ እናምናለን ፣ ምክንያቱም ያለው ስርዓት የእኛን ማኅበረሰብ የሚደግፍና የሚያግዙ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ ይህ እርዳታ ልግስና አይደለም ፣ ለእኛ የህብረተሰባችንን ፍላጎቶች በቀጥታ ማቃለል አስፈላጊ የማህበራዊ ለውጥ መሠረት ነው ።

ይህ ሥራ የሚመራው ጠንካራ በሆኑ ትስስሮች ላይ የተመሰረተ ግንኙነቶች አማካይነት ነው ፡፡

ገንዘብ ማሰባሰብ እና የማመልከቻው ሂደት ከዕቅዱ አንሳሸ ቡድን ውጭ ባሉ የታመኑ የማህበረሰብ መሪዎች በሚደረግ የማረጋገጫና ቁጥጥር ኮሚቴ ይካሄዳል። እኛን ጨምሮ - በርካታ በ GTA ዙሪያ የሚገኙ ኤርትራዊያን እና የኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ድጋፍ እና መመሪያ አለን ፣ ማለትም Art and Health አርት እና ጤና ፣ Young Diplomats የወጣት ዲፕሎማቶች ፣

ኒው ናክፋ New Nakfa፣ Midtown ሚድታውን ፣ p2p የሰዎች AID ድርጅት ካናዳ እና የጥቁር ወጣት ባለሙያዎች ማሕበር



በቶሮንቶና አካባቢዋ ለሚኖሩ ኤርትራዊያን እና ኢትዮጵያውያን የአንድ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ 10,000 ዶላር መዋጬ እናስበስባለን



የማኅበረሰቦቻችን ደኅንነት ለመጠበቅ አካላዊ ርቀትን ደንብ መከተል አስፈላጊ የጤና ጥበቃ ምላሽ ነው ፣ ነገር ግን የኮሮና ወረርሽኝ ያስከተለውን ስጋት ለመከላከል የተወስዱ በርካታ እርምጃዎች ብዙ ቢኖርም የጤና ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖዎች እንዳሉትም እናውቃለን ፡፡

በ GTA ቶሮንቶና አካባቢ ውስጥ ከሚገኙት ታላላቅ የጥቁር አፍሪካዊያን ስደተኞች ማህበረሰብ እኛ አንዱ እንደ መሆናችን መጠን አብዛኛው ኤርትራዊያን እና ኢትዮጵያውያን ከ COVID-19 በፊትም በቂ መኖሪያ ፣ ሥራና የጤና አገልግሎቶችን ለማግኘትእንደሚታገሉ እናውቃለን ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ CERB እና CESB ዝቅተኛ የገንዘብ ገቢ ፤ ደካማ የኢኮኖሚ አቅም ላላቸው ሰራተኞች ፣የውጭ ዜግነት ያላቸው ተማሪዎች ፣ አርቲስቶች እና ዜግነት የሌላቸውን የማህበረሰብ አባላት መድረስ አለመቻሉን እናውቃለን ፡፡ በተጨማሪ አካላዊ ርቀት የሰዎችን የአኗኗር ዘይቤ እንዳባባሰው እናውቃለን ፤ አንዳንዶች የመኖሪያ ቤተ እጦት እያጋጠማቸው እንዳለ እንዲሁም ሌሎች የጾታ በደል በሚፈጠርባቸው ሁኔታዎች ተገደው የሚቆዪ አሉ ፡፡ COVID-19 ሁሌም ነባር በቶሮንቶ ኅብረተሰብ ውስጥ የሠረፀውን ጥልቅ ማህበራዊ ክፍፍል እያጋለጠ ይገኛል።

የፖሊስ አመጽ ፣ የመዋእለ ሕጻናት ውድነት፣ የገቢ አለመመጣጠን ፣ የመኖሪያ ቤት እጥረትና ውድነት እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች እኛ የምናውቀው የቶሮንቶ ገጽታ አካል ሆነው ቆይተዋል። በአሁኑ ጊዜ ለወረርሽኙ በሽታ የተስጡ ምላሾች መቋቋም ለፈለግነው የሕልውና ተግዳሮት ጉዳይ ሙሉ በሙሉ ብቁ መፍትሄ አይደሉም ፡፡ በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ሰዎች ለመደገፍ የሚያስችል የኢኮኖሚ ክፍፍል ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ያስፈልጋል።


ስለዚህም የምንሰራው የሚከተለውን ይሆናል:

ወረርሽኝ ባስከተለው ቀውስ የተጠቁ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ግለሰቦች እና ቤተሰቦችን በመቅረብ በትብብር ለመስራት ወደ ማህበረሰባችን እየመጣን ነን ፡፡ ሰዎች የሚፈልጉትን ለማግኝገት መንግሥት ላይ ብቻ መታማመን አንችልም ፡፡ እኛ በህብረተሰቡ ውስጥ የምንመሠርተው የራሳችንን መፍትሄዎች እየፈጠርን የኑሮ ማጎልበቻ ድጋፎችን እውን ለማድረግ መጣር አለብን፡፡

ከዚህ ተነሳሽነት የሚገኘውን ገንዘብ በቀጥታ ሥራቸውና ህይወታቸው በ COVID-19 ለተጠቁ ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ማድረስ፡፡ ከዚህ ፈንድ ገንዘብ በማኅበረሰባችን ውስጥ በጣም ከፍ ያለ ጉዳት ለደረስባቸው ስዎች በፍጥነት ይስጣል፡፡

ኑ ከእኛ ጋር ለመሥራት ተቀላቀሉ!

በቶሮንቶና አካባቢዋ ለሚኖሩ ኤርትራዊያን እና ኢትዮጵያውያን የአንድ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ 5,000 ዶላር መዋጬ እናስበስባለን፡፡

የሚከማቸው ገንዘብ በሞላ በወረርሽኙ ምክንያት መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ችግር ላጋጠማቸው ይሠጣል፡፡ አስቸኳይ ፍላጎቶች የሚያካትቱት ግን በዚህ ብቻ የተወስኑ አይደሉም-

ቤት ኪራይ ፣ መድሃኒት ፣ ምግብ እና ውሃ ፣ የአእምሮ እና የአካል እንክብካቤ ዋጋ ግሽበት አለ፡

አመልካቾች የኑሮ ሁኔታቸውንበዝርዝር እንዲገልጹ አይጠየቁም ፣ ነገር ግን የሚከተሉትን ሁለት የብቁነት መሠረት በማድረግ ገንዘብ ይቀበላሉ።



© 2020 ERI-ETHIO COVID-19 SOLIDARITY FUND | All rights reserved. Some material has been re-purposed from the #ShareMyCheque campaign. Visit ShareMyCheque.org to learn more. Thank you to all our volunteer translators from across the world!
Powered by Webnode
Create your website for free! This website was made with Webnode. Create your own for free today! Get started